የሱቅ ሽያጭ፣ የዕቃ ክምችት እና የብድር መቆጣጠሪያ — ያለ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ይሰራል
Offline Shop Management, Inventory & Credit Tracking
አፑን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱ የንግድዎን አይነት ይመርጣሉ፤ መተግበሪያውም ለስራዎ የሚያስፈልጉ መስኮችን እና ዝርዝሮችን ብቻ ያዘጋጅልዎታል።
ዝርዝር መመሪያ ለማየት → የአጠቃቀም መመሪያ
ሙከራው ሲጠናቀቅ እስከ 30 ምርቶች እና 1 ሱቅ በነጻ መጠቀም መቀጠል ይችላሉ። / The free tier supports up to 30 products and 1 shop indefinitely.
ሙሉ ፍቃድ (License) ለመግዛት ወይም ለበለጠ መረጃ ያግኙን፦ / To buy a licence or ask anything:
ሁሉም መረጃዎች በስልክዎ ውስጣዊ ማህደረ ትውስታ ላይ ብቻ ይቀመጣሉ። ወደ ሰርቨር የሚላከው እርስዎ ባክአፕ (Backup) ሲያደርጉ ብቻ ሲሆን፣ እሱም በሚስጥር ቁጥር (Encrypted) ስለሚታገድ እርስዎ ብቻ በሚያውቁት ኮድ እንጂ እኛም ብንሆን ልናየው አንችልም።
All data is stored directly on your phone. If you choose to back up, an encrypted copy is sent to our server; only you have the decryption key.
በቀላሉ አዲሱ ስልክዎ ላይ አፑን ይጫኑ፤ በመጀመሪያ የተሰጠዎትን ባለ 16 ፊደል/ቁጥር የመልሶ ማግኛ ኮድ (Recovery Code) በማስገባት ሁሉንም መረጃዎች በቅጽበት መልሰው ማግኘት ይችላሉ። ስለዚህ የመልሶ ማግኛ ኮድዎን በጥንቃቄ ያስቀምጡ።
Simply install the app on your new device and enter your secret recovery code. All your data will be restored. Make sure to keep your code safe.
ቀጥታ ዝመናዎችን (Updates) በፍጥነት ለእርስዎ ለማድረስ እና ተጨማሪ ክፍያዎችን ለማስቀረት ከአስተማማኙ ድረ-ገጻችን በቀጥታ እናቀርባለን። ስልክዎ ሲጭኑ "ከዚህ ምንጭ መጫን ፍቀድ" (Allow from this source) ብሎ ቢጠይቅዎ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለውም፤ ፈቅደው መጫን ይችላሉ።
We distribute directly from our website to provide fast updates without extra third-party costs. Enabling "Allow from this source" on Android is safe and normal.
አፑን ለ 30 ቀናት ሙሉ አገልግሎቱን በነጻ ሞክረው መመልከት ይችላሉ። ከዚያ በኋላ እስከ 30 ምርቶች እና 1 ሱቅ በነጻ ሁሌም መጠቀም ይችላሉ፤ ብዙ ምርቶችን ለመመዝገብ እና ተጨማሪ ሱቆችን ለማስተዳደር ግን አነስተኛ የፈቃድ (License) ክፍያ መክፈል ይኖርብዎታል።
Enjoy full access with a 30-day free trial. Afterwards, you can continue on the free plan (up to 30 products, 1 shop), or upgrade to unlock unlimited capacity.
በመተግበሪያው ውስጥ ፈቃድ ማያ ውስጥ የስልክዎን መለያ (ID) ይቅዱ እና ለእኛ ይላኩ። ክፍያ ካረጋገጥን በኋላ የማግበሪያ ኮድ እንሰጥዎታለን ወይም ፈቃዱን እናግብርልዎታለን፤ ኮዱን በፈቃድ ማያ ያስገቡ፣ ወይም ኢንተርኔት ላይ "ሁኔታ አድስ" ይንኩ። ስልክ ከተቀየረ ፈቃዱን ወደ አዲሱ ስልክ እናስተላልፋለን።
Open the Licence screen in the app, copy your phone ID and send it to us. Once payment is confirmed we send an activation code or activate it for you; enter the code in the Licence screen, or tap "Refresh status" while online. If you change phones we can move the licence to the new one.
አዎ። ዋናው ስልክ ባክአፕ በራሱ ወደ ደመና ይልካል፤ ሁለተኛው ስልክ በ "የሱቅ ክትትል" ተመሳሳይ ኮድ በማስገባት የሱቁን ሁኔታ ለማንበብ ብቻ ይመለከታል (ምንም መቀየር አይችልም)።
Yes. The main phone backs up automatically; a second phone can enter the same code under "Follow shop" to view the shop read-only (it cannot change anything).
3af58403221b5b41f2ffa26a5a119db455b6237084cc3a64f2243f2c78f6f60f