የአጠቃቀም መመሪያ

ከመጫን እስከ ባክአፕ — በደረጃ በደረጃ።
Step-by-step user guide

ማውጫ / Contents

📲 መጫን · Install

  1. ከ ማውረጃ ገጹ "መተግበሪያውን አውርድ" ይንኩ።
  2. የወረደውን ፋይል ይክፈቱ፤ "ከዚህ ምንጭ መጫን ፍቀድ" ይጠይቅዎታል — ያብሩት።
  3. Play Protect ማስጠንቀቂያ ካሳየ "ለማንኛውም ጫን" ይምረጡ።
  4. የ 30 ቀን ነጻ ሙከራ መተግበሪያውን ሲከፍቱ ይጀምራል።

🏪 የመጀመሪያ ዝግጅት · First setup

  1. መተግበሪያውን ሲከፍቱ የሱቅዎን ዓይነት ይምረጡ (ፋርማሲ፣ ግሮሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ…)።
  2. ፋርማሲ ከሆነ ጊዜ ማብቂያ (expiry) እና batch ይኖራል፤ ግሮሰሪ እና ኮስሜቲክስ expiry አላቸው፤ ኤሌክትሮኒክስ ዋስትና በደረሰኝ ላይ ያሳያል።
  3. የሱቅ ዓይነት በኋላ ከቅንብሮች ቢቀይሩ ዳታዎ አይጠፋም።
  4. ብዙ ምርት ካለዎት "ምርቶችን ከፋይል አስገባ" ይጠቀሙ (Excel ፋይልዎን በ CSV አድርገው ያስቀምጡ)።

📦 ምርቶች እና ስቶክ · Products & stock

  1. አዲስ ምርት፦ ስም · ምድብ · የግዢ ዋጋ · የመሸጫ ዋጋ · ብዛት ያስገቡ።
  2. የግዢ ዋጋ እና ትርፍ % ሲያስገቡ መሸጫ ዋጋው በራሱ ይሞላል።
  3. ስቶክ ለመጨመር ምርቱ ላይ "ስቶክ ጨምር" ይንኩ።
  4. አቅራቢ ከመረጡ ግዢ ይመዘገባል። አቅራቢ ሳይመርጡ ስቶክ ብቻ ይጨምራል፤ ካዝና አይቀንስም።

🛒 ሽያጭ · Selling

  1. ምርት ይምረጡ ወይም ባርኮድ ስካን ያድርጉ።
  2. ብዙ ዕቃ ካለ "ጥምር ሽያጭ" ይጠቀሙ።
  3. ቅናሽ በብር ወይም በ % ማስገባት ይቻላል።
  4. ክፍያ ይምረጡ፦ ጥሬ · ባንክ · ሞባይል · ብድር። ብድር ሲሆን ደንበኛ መምረጥ ግዴታ ነው።
  5. የ PDF ደረሰኝ በቀጥታ ለደንበኛ ማጋራት ይችላሉ። ጊዜው ያለፈበት ምርት አይሸጥም።

🧾 ደንበኞች እና ብድር · Customers & credit

  1. ብድር ሽያጭ ሲያደርጉ የደንበኛው ዕዳ ይጨምራል።
  2. ክፍያ ሲመዘግቡ ዕዳው ይቀንሳል፤ ክፍያው በካዝና እንደ ጥሬ ገንዘብ ይቆጠራል።
  3. ደንበኛ ተመላሽ ዕቃ ሲያመጣ "ተመላሽ" ይመዝግቡ፤ ስቶክ እና ሪፖርት ራሱ ይስተካከላል።

📊 የዕለት ሂሳብ እና ሪፖርት · Daily closing & reports

  1. የዕለት ሂሳብ የዛሬውን ሽያጭ፣ ትርፍ እና ወጪ ያሳያል። የተጣራ ትርፍ = ትርፍ − ወጪ።
  2. "የመነሻ ጥሬ ገንዘብ" ጠዋት በእጅ ይሞላል (አማራጭ)፤ ለነገ አይቀመጥም።
  3. "በእጅ የተቆጠረ" ሲያስገቡ ብልጫ ወይም ጉድለት ይታያል።
  4. ሪፖርቶችን ወደ Excel ማውጣት ይችላሉ።

👥 ባለቤት እና ሻጭ (ብዙ ተጠቃሚ) · Owner & cashier

  1. ቅንብሮች → ብዙ ተጠቃሚዎች → አንቃ።
  2. የባለቤት PIN (4–8 አሃዝ) ያስገቡ።
  3. "ተጠቃሚዎችን አስተዳድር" ላይ ሻጮችን ይጨምሩ።
  4. ባለቤት ሁሉንም ያደርጋል (ቅንብሮች፣ ሪፖርት፣ ሰርዝ፣ ባክአፕ)፤ ሻጭ በዋናነት ሽያጭ እና ስቶክ ብቻ።
  5. መተግበሪያው ከ60 ሰከንድ በላይ ከተዘጋ እንደገና PIN ይጠይቃል።

🔑 ፈቃድ ማግበር · Activate a licence

  1. መተግበሪያው ውስጥ "ፈቃድ" ይክፈቱ፤ የስልክዎን መለያ (ID) "ቅዳ" ይንኩ።
  2. ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ID ን ለእኛ ይላኩ (ከታች ያለውን መገናኛ ይጠቀሙ)።
  3. የማግበሪያ ኮድ ከተሰጠዎት "የማግበሪያ ኮድ" ውስጥ ለጥፈው "አግብር" ይንኩ። ኮዱ ለዚህ ስልክ ብቻ ነው የሚሰራው።
  4. ወይም ኢንተርኔት ባለበት "ሁኔታ አድስ" ይንኩ።
  5. ኮድዎን ለራስዎ ያስቀምጡ (ቅዳ ወይም አጋራ) — ስልክ ቢቀየር እንዲያግዝ።

☁️ ባክአፕ እና መልሶ ማግኘት · Backup & restore

  1. በስልኩ ላይ በየቀኑ ራሱ ባክአፕ ይይዛል። በእጅ ለማድረግ፦ "Backup እና Restore"።
  2. ፈቃድ ካለዎት "የደመና ባክአፕ" → "አሁን ባክአፕ አድርግ" ይንኩ። የ 16 ፊደል/ቁጥር የመልሶ ማግኛ ኮድ ይሰጥዎታል።
  3. ኮዱን ለራስዎ ይላኩ (ለምሳሌ Telegram Saved Messages) ወይም ይጻፉት። ባክአፑ በዚህ ኮድ የተመሰጠረ ነው፤ ከጠፋ ማንም (እኛም) ሊመልሰው አይችልም።
  4. ስልክ ቢጠፋ፦ አዲስ ስልክ ላይ መተግበሪያ ጫኑ → "Backup እና Restore" → "ከደመና መልስ" → ኮዱን ያስገቡ።
  5. መልሶ ማግኘት አሁን ያለውን ዳታ ይተካል (ከመተካቱ በፊት ይቀመጣል)።

👁 ሁለተኛ ስልክ — የሱቅ ክትትል · Second phone — Follow shop

  1. በዋናው ስልክ የደመና ባክአፕ ያድርጉ፣ "በራስ ሰር ባክአፕ" ያብሩ (ዳታ ሲቀየር ከ90 ሰከንድ በኋላ ይጫናል)።
  2. በሁለተኛው ስልክ መተግበሪያውን ጭነው ዋና ምናሌ → "የሱቅ ክትትል (ከሌላ ስልክ)" ይክፈቱ።
  3. ተመሳሳዩን የመልሶ ማግኛ ኮድ ያስገቡ።
  4. ሁለተኛው ስልክ ሱቁን ለማንበብ ብቻ ይመለከታል፤ ምንም መቀየር ወይም መጫን አይችልም።

⬆️ ማሻሻል (Update) · Updating

  1. አዲስ ስሪት ሲወጣ ከዚህ ገጽ አውርደው በአሮጌው ላይ ይጫኑ።
  2. ዳታዎ እንዳለ ይቆያል። ለጥንቃቄ ከማሻሻልዎ በፊት ባክአፕ ያድርጉ።

እገዛ ይፈልጋሉ? / Need help?

በመተግበሪያው ውስጥ "ድጋፍ" ውስጥ መልዕክት መላክ ይችላሉ፤ ወይም በቀጥታ ያግኙን፦

@mskrawraris

ግላዊነት (Privacy) →